# ሜዶን፣ ሜዶናውያን ሜዶን ከአሦርና ከባቢሎን በስተ ምሥራቅ፣ ከኤላምና ከፋርስ በስተ ሰሜን የነበረ ትንታዊ መንግሥት ነው። የነበረበት ቦታ በአሁኑ ዘመን ቱርክ፣ ኢራን፣ ሶርያ፣ ኢራቅና አፍጋኒስታን ያሉበትን በክፊል ያካትት ነበር። * በሜዶን መንግሥት የነበሩ ሰዎች ሜዶናውያን ይባሉ ነበ።ር * ሜዶናውያን ከፋርስ ጋር በጣም ይቀራረቡ ነበር፤ ሁለቱ መንግሥታት በአንድነት ሆነው የባቢሎንን መንግሥት አሸንፈዋል። * ሜዶናዊው ዳርዮስ በባቢሎን የወረረው ነቢዩ ዳንኤል እዚያ እያለ ነበር።