# ሉቃስ ሉቃስ አዲስ ኪዳን ውስጥ ያሉ ሁለት መጻሕፍት የሉቃስ ወንጌልና የሐዋርያት ሥራ ጸሐፊ ነው። * ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው መልእክት ሉቃስ ሐኪም እንደ ነበር ጳውሎስ አመልክቷል። በሌሎች ሁለት መልእክቶቹም ጳውሎስ ሉቃስን ጠቅሷል። * ሉቃስ በሁለት ሐዋርያዊ ጉዞዎቹ ከጳውሎስ ጋር አብሮ ነበር፣ በሥራውም ረድቶታል። * አንዳንድ የጥንት ቤተ ክርስቲያን ጽሑፎች ሉቃስ የተወለደው በሶርያ ባለችው አንጾኪያ ከተማ እንደ ነበር ያመለክታሉ።