# ኢዮአታም ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢዮአታም ተብለው የሚጠሩ ሦስት ሰዎች አሉ። * ኢዮአታም የሚባለው አንዱ የጌዴዎን ታናሽ ልጅ ነበር። ሌሎች ወንድሞቻቸውን ሁሉ የገደለው ታላቅ ወንድሙ አቤሜሌክን ድል ለማድረግ ኢዮአታም ተባብሮአል። * ሌላው ኢዮአታም የሚባል ሰው ከአባቱ ከዖዝያን ሞት በኋላ ለአስራ ስድስት ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የነበረ ነው። * እንደአባቱ ሁሉ ኢዮአታም ለእግዚአብሔር የታዘዘ መልካም ንጉሥ ነበር። * ይሁን እንጂ እንደአባቱ ሁሉ ንጉሥ ኢዮአታም ጣዖት የሚመለክባቸው ቦታዎችን አላጠፋም፤ ይህም በኋላ ላይ ሕዝቡ እንደገና ጣዖት ወደማምለክ እንዲመለሱ አድርጓል። የጣዖት አምልኮ ሌላው ውጤት የኢዮአታም ልጅ አካዝ ክፉ ንጉሥ መሆኑ ነበር። * ኢዮአታም የማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ባለው የኢየሱስ ክርስቶስ የዘር ሐረግ ከተዘርዘሩት ጥንተ አባቶች አንዱ ነበር።