# ዮሴፍ (ብሉይ ኪዳን) ዮሴፍ የያዕቆብ አሥራ አንደኛ ልጅ ሲሆን፣ ለራሔል ደግሞ የመጀመሪያ ልጇ ነበር። * ዮሴፍ በአባቱ ዘንድ በጣም የተወደደ ልጅ ስለነበር ወንድሞቹ ቀኑበት፤ ለባርነትም ሸጡት። * በግብፅ አገር ባርያና እስረኛ መሆንን ጨምሮ ዮሴፍ በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ አልፏል፤ ያም ሆኖ ግን ለእግዚአብሔር ታማኝነቱን ጠብቋል። * እግዚአብሔር ግብፅ ውስጥ ሁለተኛ ወደነበረው የሥልጣን ደረጃ አደረሰው፤ ግብፅንና የአባቱን ቤተሰቦች በራብ ከመሞት እንዲያድን ተጠቀመበት።