# ዮሴፍ (አዲስ ኪዳን) ዮሴፍ የማርያም እጮኛ የነበረ ሲሆን፣ እንደ አባት ኢየሱስን አሳድጓል። * ዮሴፍ የንጉሥ ዳዊት ዘር ነበር። * ዮሴፍ የመሲሑ ኢየሱስ እናት እንድትሆን እግዚአብሔር ከመረጣት ድንግል ጋር ተጫጭቶ ነበር። * ማርያም በተአምር እንድትፀንስ ያደረገ መንፈስ ቅዱስ መሆኑንና ከማርያም የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን መልአክ ለዮሴፍ ነገረው። * ዮሴፍ ምልአኩ የነገረውን አመነ፤ ማርያምን ወደቤቱ በመውሰድም ለእግዚአብሔር ታዘዘ። * ኢየሱስ እስኪወለድ ድረስ ዮሴፍ ማርያም በድንግልና እንድትቆይ አደረገ።