# ዮሐንስ (ማርቆስ) ዮሐንስ ማርቆስ በሐዋርያዊ ተልዕኮው ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር ከተጓዙ ሰዎች አንዱ ሲሆን፣ ማርቆስ ተብሎ ይጠራል። * ዮሐንስ ማርቆስ በመጀመሪያው ሐዋርያዊ ተልዕኳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር አብሮ ተጉዞ ነበር። * ጴጥሮስ በኢየሩሳሌም በታሰረ ጊዜ አማኞች ለእርሱ እየጸለዩ የነበረው የዮሐንስ ማርቆስ እናት ቤት ውስጥ ነበር። * ማርቆስ ከመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት አንዱ ባይሆንም ከሐዋርያው ጳውሎስና ጴጥሮስ ተምሯል፤ በአገልግሎትም ከእነርሱ ጋር ሠርቷል።