# ኢይዝራኤል ኢይዝራኤል ከጨው ባሕር ደቡብ ምዕራብ ነገድ ክልል ውስጥ የነበረች በጣም ጠቃሚ የእስራኤል ከተማ ስም ነው። ጥቂት የእስራኤል ንጉሦች ቤተመንግሥታቸውን የሠሩት እዚያ ነበር። * የኢይዝራኤል ከተማ የመጊዶ ሜዳማ ቦታ ምዕራባዊ ጫፎች ከሆኑት አንዷ ስትሆን የኢይዝራኤል ሸለቆ ተብሎም ይጠራል። * የናቡቴ ወይን እርሻ የነበረው በኢይዝራኤል አክዓብ ቤተመንግሥት አጠገብ ነበር። ነብዩ ኤልያስ እዚያ በነበረው አክዓብ ላይ ትንቢት ተናገረ። * ክፉዋ የአክዓብ ሚስት ኤልዛቤል የተገደለችው በኢይዝራኤል ነበር። * ጥቂት ጦርነቶችን ጨምሮ በዚህ ከተማ ሌሎችም ሁነኛ ጉዳዮች ተፈጽመዋል።