# ኤርምያስ ኤርምያስ በይሁዳ መንግሥት የእግዚአብሔር ነብይ ነበር። * እንደ አብዛኞቹ ነብያት ሁሉ ኤርምያስ እግዚአብሔር በኀጢአታቸው ሕዝቡን እንደሚቀጣ ዘወትር ሕዝቡን ማስጠንቀቅ ነበረበት። * ባቢሎን ኢየሩሳሌምን እንደምትይዝ ኤርምያስ ትንቢት ተናግሮ ነበር፤ ይህ ግን የይሁዳን ሕዝብ አስቆጣ። ስለዚህም እዚያው እንዲሞት ደረቅ ጉድጓድ ውስጥ ከተቱት። ይሁን እንጂ፣ የይሁዳ ንጉሥ ኤርምያስን ከጉድጓድ እንዲያወጡት አዘዘ።