# ኢዮአቄም ኢዮአቄም ከ60 ዓቅክ ጀምሮ በይሁዳ መንግሥት ላይ የነገሠ በጣም ክፉ ነጉሥ ነበር። እርሱ የንጉሥ ልጅ ነበር። መጀመሪያ ላይ ኤልያቄም ይባል ነበር። * የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ፥ የኤልያቄምን ስም ኢዮአቄም ወደሚል ለውጦ የይሁዳ ንጉሥ አደረገው። * ፈርዖን ኒካዑ ለግብፅ ግብር እንዲከፈል ኢዮአቄምን አስገደደ። * በኋላ ላይ ይሁዳ በንጉሥ ናቡከደነፆር ስትወረር ወደ ባቢሎን ከተወሰዱት ሰዎች አንዱ ኢዮአቄም ነበር። * ኢዮአቄም ለእግዚአብሔር የማይታዘዝና እንዲያውም የይሁዳ ሕዝብ ያህዌን እንዳያመልክ ያደረገ ንጉሥ ነበር። ነብዩ ኤርምያስ በእርሱ ላይ ትንቢት ተናግሮ ነበር።