# ዮዳሔ ዮዳሔ ንጉሥ ለመሆን እስከበቃበት ድረስ የንጉሥ አካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ደብቆ ያቆየውና የተከላከለለት ካህን ነበር። * ቤተመቅደሱ ውስጥ በነበሩ ሰዎች ንጉሥ እንዲሆን በታወጀ ጊዜ፥ ዮዳሔ ወጣቱ ኢዮአስን የሚጠብቁ በመቶ የሚቆጠሩ ጠባቂዎች አዘጋጀ። * የበኣል መሠዊያዎችን ሁሉ እንዲያጠፉ ሕዝቡን የመራ ዮዳሔ ነበር። * በተቀረው የህይወት ዘመኑ ካህኑ ዮዳሔ ለእግዚአብሔር እንደታዘዘና ሕዝቡን በመልካም መንገድ እንዲገዛ ንጉሥ ኢዮአስን ሲረዳው ነበር። * ዮዳሔ ተብሎ የሚጠራ ሌላ ሰው የበናያስ አባት ነበር።