# እስማኤል እስማኤል የአብርሃምና የሥራ አገልጋይ የነበረችው የአጋር ልጅ ነው። * “እስማኤል” እግዚአብሔር ይሰማል ማለት ነው። * እስማኤል ስለ እርሱና ስለ የወደ ፊት ሕይወቱ እግዚአብሔር ለአጋር የገባላትን መለኮትዊ ተስፋ ጥቅም ተቀብሏል። * ይሁን እንጂ፣ በእርሱ በኩል ዘሮቹን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደሚያበዛ ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ የሚፈጸምበት ልጅ እስማኤል አይደለም።