# ኮሬብ የኮሬብ ተራራ አሥሩ ትእዛዞች የተጻፈባቸው ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠበት የሲና ተራራ ሌላ ስም ነው። * በጎቹን እየጠበቀ ሳለ ሙሴ የሚቃጠለውን ቁጥቋጦች ያየው በኮሬብ ነበር። * ዐለቱን በበትሩ በመታው ውሃ ለጠማቸው እስራኤላውያን ውሃ እንደሚያወጣ እግዚአብሔር ለሙሴ የነገረው በኮሬብ ነበር። * የዚህ ተራራ ትክክለኛ ቦታ የት እንደ ሆነ አይታወቅም፤ ይሁን እንጂ፣ የሲና ባሕረ ገብ ደቡባዊ ክፍል ላይ ሊሆን እንደሚችል ይታሰባል። * አንዳንድ ምሁራን፣ “ኮሬብ” ትክክለኛ የተራራ ስም ሲሆን፣ “የሲና ተራራ” የሚለው ግን ሲና በረሐ ውስጥ የነበረውን ተራራው የነበረበትን ቦታ ያመለክታል በማለት ያስባሉ።