# ጎልጎታ “ጎልጎታ” ኢየሱስ የተሰቀለበት ቦታ ስም ነው። ቃሉ የመጣው፣ “የራስ ቅል” ወይም፣ “የራስ ቅል ቦታ” ከተሰኙ የአረማይክ ቃል ነው። * ጎልጎታ ከኢየሩሳሌም ከተማ ቅጥር ውጭ ባለው የደብረ ዘይት ተራራ ክፍል በሆነ ቦታ ይገኝ ነበር። * አንዳንድ ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ጎልጎታን፣ “ቀራንዮ” በማለት ይተረጉሙታል፤ ይህም በላቲን የራስ ቅል ማለት ነው።