# ገላትያ አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ገላትያ በአሁኑ ዘመን ማዕከላዊ ቱርክ የሚባለው ቦታ ላይ ትገኝ የነበረች የሮም ከተማ ነበረች። * ሐዋርያው ጳውሎስ ገላትያ ከተማ ውስጥ ይኖሩ ለነበሩ ክርስቲያኖች የገላትያን መልእክት ጽፎላቸው ነበር። ይህ መልእክት አዲስ ኪዳን ውስጥ ያለው የገላትያ መልእክት ነው። * ከአሕዛብ ወገን የነበሩት የገላትያ ክርስቲያኖች አንዳንድ የሙሴን ሕጎች መፈጸም እንደሚገባቸው ከአይሁድ ክርስቲያኖች ተጽዕኖ ደርሶባቸው ነበር። * ጳውሎስ መልእክቱን ለገላትያ ሰዎች ከጻፈበት ምክንያት አንዱ ድነት በጸጋ እንጂ በሥራ አለመሆኑን በድጋሚ ለማስረገጥ ነበር።