# ኤሳው ኤሳው ይስሐቅ ከርብቃ ከወለደቻቸው መንታ ልጆች ታላቁ ነበር፣ መንታ ወንድሙ ያዕቆብ ነበር። * ኤሳው በምስር ወጥ ብኩርናውን ለወንድሙ ለያዕቆብ ሸጠ። * ኤሳው የመጀመሪያ ልጅ በመሆኑ፣ አባቱ የተለየ በረከት ይሰጠው ነበር። ይሁን እንጂ፣ ያዕቆብ አባቱን በማታለል ያንን በረከት ወሰደ። መጀመሪያ ላይ ኤሳው በጣም ተቆጥቶ ያዕቆብን መግደል ፈልጎ ነበር፤ በኋላ ግን ይቅርታ አደረገለት። * ኤሳው ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩት። የእርሱ ዘሮች በምድረ ከነዓን የሚኖሩ በጣም ብዛት ያለው ሕዝብ ሆነዋል።