# ኤደን፣ ኤደን ገነት በጥንት ዘመን ኤደን እግዚአብሔር የመጀመሪያውን ወንድና ሴት ያኖረበት የአትክልት ቦታ ያለው አካባቢ ነበር። * አዳምና ሔዋን የነበሩበት አትክልት ቦታ ከኤደን ጥቂት ክፍሉ ብቻ ነበር። * ኤደን የነበረበትን ትክክለኛ አካባቢ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፤ የኤፍራጥስና የጤግሮስ ወንዝ ያጠጡት እንደ ነበር ግን ተገልጿል። * ኤደን የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን፣ “በጣም ደስ መሰኘት” የሚል ትርጕም አለው።