# ቆርኔሌዎስ ቆርኔሌዎስ በትውልድ አይሁድ ያልሆነ የሮም ወታደሮች ባለ ሥልጣን ነበር። * ዘወትር ለእግዚአብሔር ይጸልይ ነበር፤ ለድኾች ምጽዋት የሚሰጥ ደግ ሰው ነበር። * ቆርኔሎዎስና ቤተ ሰቡ ሐዋርያው ጴጥሮስ የሚያስተምረውን ወንጌል ሰምተው በኢየሱስ አመኑ። * የቆርኔሌዎስ ቤተ ሰቦች አይሁድ ያልነበሩ የመጀመሪያዎቹ አማኞች ነበሩ። * ይህም ኢየሱስ እርሱ የመጣው አረማውያንን ጨምሮ ሰዎችን ሁሉ ለማዳን መሆኑን ለኢየሱስ ተከታዮች ግልጽ አደረገላቸው።