# ኪልቅያ ኪልቅያ አሁን የዘመኑ ቱርክ ካለችበት ደቡብ ምሥራቃዊ ክፍል የነበረች አነስተኛ የሮማውያን አውራጃ ነበረች። ከኤጂያን ባሕር ጋር ይዋሰናል። * ሐዋርያው ጳውሎስ ኪልቅያ ውስጥ የነበረችው የጠርሴስ ሰው ነበር። * በደማስቆ መንገድ ከኢየሱስ ጋር ከተገናኘ በኋላ ጳውሎስ በኪልቅያ ጥቂት ዓመቶች አሳልፎ ነበር። * ከኪልቅያ ከመጡ አይሁድ መካከል አንዳንዶቹ እስጢፋኖስን ተቀውመው ነበር፤ በድንጋይ ቀጥቅጠው እንዲገድሉትም ሕዝቡን አንሳሥተዋል።