# ካሌብ ካሌብ የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ሙሴ ከላካቸው አሥራ ሁለት እስራኤላውያን አንዱ ነበር። * ከእነርሱ ትውልድ ወደ ከነዓን ምድር እንዲገቡ እግዚአብሔር የፈቀደላቸው ሰዎች ኢያሱና ካሌብ ብቻ ነበር። * የኬብሮን ምድር ለእርሱና ለቤተ ሰቡ እንድትሰጥ ካሌብ ጠየቀ። እዚያ የነበሩ ሰዎችን እንዲያሸንፍ እግዚአብሔር እንደሚረዳው አውቆ ነበር።