# ቃየን ቃየንና ታናሽ ወንድሙ አቤል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ የመጀመሪያ የአዳምና የሔዋን ልጆች ናቸው። * ቃየን የምግብ እህሎች የሚያመርት ገበሬ ሲሆን፣ አቤል ግን በጎች የሚጠብቅ እረኛ ነበር። * እግዚአብሔር የአቤልን መሥዋዕት ቢቀበልም፣ የቃየልን መሥዋዕት ግን ባለመቀበሉ በቅናት ተነሳሥቶ ቃየን ወንድሙ አቤልን ገደለው። * እርሱን ለመቅጣት እግዚአብሔር ቃየንን ከኤደን አባረረው ምድር በቂ እህል እንደማትሰጠውም ተናገረ። * እርሱ በምድር ላይ በሚንከራተትበት ጊዜ ሌሎች ሰዎች እንዳይገድሉት እግዚአብሔር እንደሚጠብቀው ምልክት የሚሆን ግንባሩ ላይ አደረገ።