# ቀያፋ ቀያፋ መጥምቁ ዮሐንስና ኢየሱስ ባገለገሉበት ዘመን የእስራኤል ሊቀ ካህን ነበር። * ኢየሱስን በመመርመርና በኋላም እንዲገደል ፍርድ በማስተላለፍ ረገድ ቀያፋ ትልቅ ድርሻ ነበረው። * ሽባውን ሰው ከፈወሱት በኋላ በታሰሩ ጊዜ ሊቀ ካህናቶቹ ሐና እና ቀያፋ የጴጥሮስና የዮሐንስ ምርመራ ላይ ተገኝተው ነበር። * ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ለሕዝቡ ሁሉ ቢሞት ይሻላል በማለት የተናገረ ቀያፋ ነበር። ኢየሱስ ለሕዝቡ በእንዴት አይነት ሁኔታ እንዲሞት በትንቢት መልክ ይህን እንዲናገር ያደረገው እግዚአብሔር ነበር።