# ብንያም ብንያም ከያዕቆብና ከሚስቱ ከራሔል የተወለደ የመጨረሻው ልጅ ነው። የስሙ ትርጉም ፥ “የቀኝ እጄ ልጅ” ማለት ነው። * ከራሔል የተወለዱ እርሱና ታላቅ ወንድሙ ዮሴፍ ብቻ ናቸው። ራሔል ብንያምን ከወለደች በኋላ ሞታለች * የብንያም ዘሮች ከአስራሁለት የእስራኤል ነገዶች አንዱ ሆነዋል * ንጉሥ ሳኦል ከእስራኤላዊው የብንያም ነገድ የተገኘ ነበር * ሐዋርያው ጳውሎስም ከብንያም ነገድ ነበር