# ቤርሳቤህ ቤርሳቤህ በዳዊት ሰራዊት ውስጥ ወታደር የነበርው የኦርዮን ሚስት ነበረች። ኦርዮን ከተገደለ በኋላ የዳዊት ሚስትና የሰሎሞን እናት ሆናለች * የኦርዮን ሚስት እያለች ዳዊት ከእርስዋ ጋር አመንዝሮ ነበር * ቤርሳቤህ ከዳዊት በፀነሰች ጊዜ ዳዊት ኦርዮን በጦርነት እንዲገደል አደረገ * ከዚያም ዳዊት ቤርሳቤህን አገባትና ልጃቸውን ወለደች * ከተወለደ ጥቂት ቀናት በኋላ ልጁ እንዲሞት በማድረግ እግዚአብሔር ዳዊትን በኃጢአቱ ቀጣው * እንደገና ቤርሳቤህ ሰሎሞን የተባለ ልጅ ወለደች፥ እርሱም አድጎ ከዳዊት በኋላ ንጉስ ሆነ