# ባሮክ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ባሮክ በመባል የሚታወቁ የተለያዩ ሰዎች አሉ * አንደኛው ባሮክ የኢየሩሳሌምን ቅጥር በመጠገን ከነህምያ ጋር አብሮ ይሠራ የነበረው የዘባይ ልጅ ባሮክ ነው * ከዚህም በላይ በነህምያ ዘመን ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ በኢየሩሳሌም መኖር ከጀመሩ መሪዎች አንዱ የነበረው የከልሐዜ ልጅ ባሮክ ነበር * ለየት ያለው የኔር ልጅ በሮክ የነብዩ ኤርምያስ ረዳት የነበረው ባሮክ ሲሆን፥ እግዚአብሔር ለነብዩ ኤርምያስ የሰጠውን መልዕክት በመጻፍና ያንን ለሕዝቡ ማንበብ በመሳሰሉ የተለያዩ ሥራዎች ኤርምያስን ረድቶታል