# አሼራ፥ የአሼራ ምስል፥ አስታሮት አሼራ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከነዓናውያን ያመልኳት የነበሩ ጣዖት ነበረች። “አስታሮት” ሌላው የአሼራ ስም ነው፥ ወይም ደግሞ ተመሳሳይ የሆነች ሌላ ጣዖት ስም ሊሆን ይችላል። * “የአሼራ ምስል” የሚለው ገለጻ፥ ይህችኑ ጣዖት እንዲወክሉ እንጨት መቅረጽን ወይም ዛፎችን ማበጀትን ያመለክታል * ብዙውን ጊዜ የአሼራ ምስል የአሼራ ባል ነው ተብሎ በሚታሰበው በዓል የተሰኘው ጣዖት መሠዊያ አጠገብ ነበር የሚቆመው። አንዳንድ ሕዝቦች በዓልን እንደፀሐይ አምላክ፥ አሼራን ወይም አስታሮትን እንደጨረቃ አምላክ ያመልኩ ነበር * የተቀረጹ የአሼራ ምስሎችን ሁሉ እንዲያጠፉ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዘዘ * ጌዴዎንን፥ ንጉሥ አሳን፥ ንጉሥ ኢዮስያስን የመሳሰሉ እስራኤላውያን መሪዎች ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ሕዝቡ እነዚህን ጣዖቶች እንዲያጠፉ አደረጉ * ይሁን እንጂ፥ ንጉሥ ሰሎሞንን፥ ንጉሥ ምናሴንና ንጉሥ አክዓብን የመሳሰሉ ሌሎች እስራኤላውያን መሪዎች የአሼራን ምስሎች ባለማስወገዳቸው ሕዝቡ እነዚህን ጣዖቶች ማምለክ ቀጠለ