# አራራት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “አራራት” ለአንድ አካባቢ፥ ለአንድ መንግሥትና የተራራ ሰንሰለት የተሰጠ ስም ነው። * “የአራራት ምድር” ምናልባት በአሁኑ ዘመን ቱርክ በሚባለው አገር ሰሜናዊ ምሥራቅ ክፍል የነበረ ቦታ ሊሆን ይችላል። * አራራት ይበልጥ የሚታወቀው የጥፋት ውሃ መቀነስ ከጀመረ በኋላ የኖህ መርከብ ያረፈችበት ተራራ ስም በመሆኑ ነው። * በዚህ ዘመን አንድ ተራራ፥ “የአራራት ተራራ” ተብሎ ከተጠራ ብዙውን ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱሱ “አራራት ተራራ” ቦታ እንደሆነ ይታሰባል።