# አካዝያስ አካዝያስ የሁለት ንጉሦች ስም ነው፤አንደኛው የእስራኤል መንግሥት ስገዛ ሌላው የይሁዳን መንግሥት ገዛ። * የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ የንጉሥ አዩራም ልጅ ነበር። ለአንድ ዓመት 841 ዓቅክ ሥልጣን ላይ ከቆየ በኃላ ኢዩ ገደለው። በኋላ ላይ የአካዝያስ ታናሽ ልጁ ኢዮአስ የንጉሥነቱን ቦታ ያዘ። * የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ የንጉሥ አክዓብ ልጅ ነበር። ለሁለት ዓመት ሥልጣን ላይ ቆየ (850-49 ዓቅክ)። ከቤተ መንግሥቱ ሰገነት ሲወድቅ በደረሰበት ጉዳት የተነሣ ሞተ በእርሱ ቦታ ወንድሙ አዮራም ነገሠ።