# አክዓብ አክዓብ ከ 875-854 ዓቅክ ስሜናዊ የእስራኤል መንግሥት ላይ ነግሦ የነበረ በጣም ክፉ ንጉሥ ነው። * ንጉሥ አክዓብ ሐሰተኛ አማልክት እንዲያመለኩ የእስራኤል ሕዝብ ላይ ተፅዕኖ አደረገ። * ነብዩ ኤልያስ ከአክአብ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ እስራኤል እንዲፈጽሙ ስላደረገው ኅጢያት ቅጣት እንዲሆን ለሦስት ዓመት ተኩል ከባድ ድርቅ እንደሚሆን ነገረው። * አክአብና ሚስቱ ኤልዛቤል ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ንጹሕ ሰዎችን መግደልን ጨምሮ ሌሎች ብዙ ክፉ ነገሮችን አድርጓል።