# አቢሜሌክ አብርሃምና ይስሐቅ በከነዓን ምድር በሚኖሩበት ዘመን አቢሜሌክ በጌራራ አካባቢ የነገሠ ንጉስ ነበር ። * ሣራ እኅቴ እንጂ ሚስቴ አይደለችም በማለት አብርሃም ንጉሥ ኢቢሜሌክን አታልሎት ነበር። * በቤርሳህ የነበሩ የውሃ ጉድጓዶች ባለቤትነትን በተመለከተ አብርሃምና አቢሜሌክ ስምምነት አድረጉ። * ርብቃ እኅቴ እንጂ ሚስቴ አይደለችም በማለት ከብዙ ዓመታት በኋላ ይስሐቅም አቤሜሌክንና ሌሎች በጌራራ የነበሩ ሰዎችን አትልሎአል። * በእርሱ በመዋሸታቸው ንጉሥ አቢሜሌክ አብርሃምን በኋላም ይስሐቅን ገሥጾአቸዋል። * አቤሜሌክ የተሰኘ ስም የነበረው ሌላው ሰው የጌዴዎን ልጅና የኢዮአታም ወንድም ነበር።እርሱ ከንጉሥ አቢሜሌክ የተለየ ሰው መሆኑን ግልጽ ለማድረግ አንዳንድ ትርጉሞች ስሙ ላይ ጥቂት ለውጥ ያደርጉ ይሆናል።