# አቢያ ከ 915- 913 ዓቅክ ነግሦ የነበር የይሁዳ ንጉሥ ስም ነው እርሱ የንጉሥ ሮብዓም ልጅ ነበር። ብሉይ ኪዳን ውስጥ አቢያ የሚል ስም የሚታወቁ ሌሎች ጥቂት ሰዎችም ነበሩ። * አቢያና ኢዩኤል የተበሉት የሳሙኤል ወንዶች ልጆችና ራስ ወዳዶች ስለ ነበሩ በእርሱ ፈንታ ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ሕዝቡ ሳሙኤልን ጠየቁ። * ሌላው አቢያ በንጉሥ ዳዊት ዘመን የቤተ መቅደሱ ካህናት ከነበሩ ሰዎች አንዱ ነበር። * አቢያ ከንጉሥ ሮብዓም ልጆች አንዱ ነበር። * ከባቢሎን ምርኮ ከዘሩባቤል ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሰ ሊቀካህን ስም አቢያ ይባል ነበር።