# ምኩራብ ምኩራብ አይሁድ እግዚአብሔርን ለማምለክ የሚሰበሰቡበት ቦታ ነው። ከጥንት ዘመን ጀምሮ ምኩራቦች ለጸሎት፣ ቅዱሳት መጽሐፍትን ለማንበብና ለመማር አገልግሎት ላይ ውለው ነበር * አይሁድ ምኩራቦችን የሠሩት ብዙዎቹ ኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ በጣም ርቀው ይኖሩ ስለነበርና ዘወትር ወደዚያ ለመሄድ ባለመቻላቸው ነበር * ኢየሱስ ዘወትር በምኩራብ ያስተምር ነበር * “ምኩራብ” የሚለው ቃል እዚያ የሚሰበሰቡ ሰዎችንም ማመልከት ይችላል