# ነፍስ ነፍስ የሰው ውስጣዊ፣ የማይታይና ዘላለማዊ ክፍል ነው። የሰውን ቁሳዊ ያልሆነ ነገር ሁሉ ይጨምራል * “ነፍስ” እና፣ “መንፈስ” ሁለት የተለያዩ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ፤ ወይም አንድን ነገር የሚያመለክቱ ሁለት የተለያዩ ቃሎች ሊሆኑ ይችላሉ * አንድ ሰው ሲሞት ነፍሱ ከሥጋው ይለያያል * አንዳንዴ፣ “ነፍስ” የሚለው ቃል የሰውን ሁለንተና ለማመልከት በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል። ለምሳሌ፣ “ኅጢአት የምታደርግ ነፍስ” ማለት፣ “ ኅጢአት የሚያደርግ ሰው” ማለት ነው፤ “ ነፍሴ ደከመች” - ማለት፣ “እኔን ደከመኝ” መለት ነው