# መለየት “መለየት” የሚለው ቃል አንድ ዓላማን ለመፈጸም ከአንድ ነገር ተለይቶ መውጣትን ያመለክታል * እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለዩ ነበሩ * መንፈስ ቅዱስ እርሱ ለሰጣቸው ሥራ በርናባስንና ጳውሎስን እንዲለዩለት በአንጾኪያ ለነበሩ ክርስቲያኖች ተናገረ * የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት የተለየ ሰው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም “ተለይቷል” * “ቅዱስ የሚለው ቃል አንዱ ትርጉም የእግዚአብሔር ለመሆንና ኅጢአተኛ ከሆነ ዓለማዊ ሕይወት የተለየ ማለት ነው * “መቀደስ” - አንድ ሰው ለእግዚአብሔር አገልግሎት መለየት ማለት ነው