# መቀደ፣ ቅድስና መቀደስ፣ ቅዱስ ይሆን ዘንድ አንድን ነገር መለየት ማለት ነው። ቅድስና ቅዱስ የመሆን ሂደት ነው * በብሉይ ኪዳን ዘመን አንዳንድ ሰዎችና አንዳንድ ነገሮች ይቀደሱ ወይም ለእግዚአብሔር አገልግሎት ይለዩ ነበር * በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎችን እግዚአብሔር እንደሚቀድስ አዲስ ኪዳን ያስተምራል። ያም ማለት ቅዱስ ያደርጋቸዋል ለአገልግሎትም ይለያቸዋል ማለት ነው * በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች በሚያደርጉት ቅዱስ ለመሆን ራሳቸውን እንዲለዩ ታዝዘዋል