# ንስሐ መግባት፣ ንስሐ “ንስሐ መግባት” እና፣ “ንስሐ” ከኀጢአት ወደ እግዚአብሔር መመለስን ያመለክታል። * ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ንስሐ መግባት” – “የአስተሳሰብ ለውጥ” ማለት ነው። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ንስሐ ማድረግ” ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው ከኀጢአት መመለስን፣ ከሰብዓዊ አስተሳሰብና ሥራ ወደ እግዚአብሔር ሐሳብና ሥራ መመለስን ነው። * ሰዎች በኀጢአታቸው ከልባቸው ንስሐ ካደረጉ እግዚአብሔር ይቅር ይላቸዋል፤ ለእርሱ መታዘዝ እንዲጀምሩም ይረዳቸዋል።