# ማስተሰሪያ “ማስተሰረያ” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ፍትሕ ለማርካት ወይም ለመፈጸምና ቁጣውን ለማስታገሥ የሚቀርብ መሥዋዕት ነው። * በኢየሱስ ክርስቶስ ደም በኩል የቀረበው መሥዋዕት የሰውን ልጅ ኀጢአት ለማስተሰረይ የቀረበ ማስተሰሪያ ነው። * የኢየሱስ መስቀል ላይ ሞት ለሰው ልጅ ኀቲአት የእግዚአብሔር ማስተሰሪያ ነው። ይህም እግዚአብሔር ሰዎችን በምሕረት እንዲያይና ለእነርሱም የዘላለም ሕይወት ለመስጠት መንገድ ሆነ።