# መጥፋት፣ ጥፋት፣ የሚጠፋ “መጥፋት” የሚለው ቃል አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ዓይነት ጥቃት ወይም አደጋ የተነሣ መሞት ወይም መደምሰስ ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለይ ለዘላለም በገሃነም መቀጣት የሚል ትርጕም አለው። * “የሚጠፋ” ሰዎች እንዲያድናቸው በኢየሱስ ማመን ባለመፈለጋቸው ለገሃነም የተወሰኑ ናቸው። * ዮሐንስ 3፡16፣ “መጥፋት” ለዘላለም በመንግሥተ ሰማይ አለመኖር መሆኑን ያስተምራል።