# ኢየሱስ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ክርስቶስ ኢየሱስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ኢየሱስ ማለት፣ “ያህዌ ያድናል” ማለት ነው። “ክርስቶስ” “የተቀባው” የሚል ትርጉም ያለው ቃል ሲሆን፣ መሲህ የሚለው ሌላ ቃል ነው። * ብዙውን ጊዜ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ወይም፣ “ክርስቶስ ኢየሱስ” በተሰኙት ሁለቱ ስሞች ይጣመራሉ። እነዚህ ስሞች የእግዚአብሔር ልጅ በኀጢአታቸው ምክንያት ሕዝቡን ከዘለዓለም ቅጣት ለማዳን የመጣ መሲህ መሆኑን አጽንዖት ይሰጣሉ። * ተአምራዊ በሆን መንገድ መንፈስ ቅዱስ ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ልጅ ሰው ሆኖ እንዲወለድ አደረገ። እርሱ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው እንዲያድን የተመደበ በመሆኑ ኢየሱስ ብለው እንዲጠሩት መልአኩ ለምድራዊ ወላጆቹ ተናግሮ ነበር። * እርሱ እግዚአብሔር መሲህ ወይም ክርስቶስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ኢየሱስ ብዙ ተአምራት አድርጓል።