# ርኩሰት “ርኩሰት” የሚለው ቃል ትርጉም፣ “ኀጢአት” ከሚለው ጋር በጣም ተመሳሳይ ቢሆንም በተለይ፣ ሆን ተብሎ የሚፈጸም በደልን ወይም ታላቅ ዐመፃን ሊያመለክት ይችላል። * “ርኩሰት” ቃል በቃል ማጣመም ወይም ማበላሸት (ሕጉን) ማለት ነው። በከፍተኛ ደረጃ የሚፈጸም የፍትሕ መዛባትን ያመለክታል። * ርኩሰት ሆን ተብሎ ሌሎች ሰዎች ላይ የሚፈጸም ጎጂ ተግባር ሊባልም ይችላል። * ርኩሰት የሚለውን ቃል መግለጽ የሚችሉ ሌሎች መንገዶች፣ “ማጣመም” እና፣ “ብልሽት” የተሰኙ ሲሆኑ ሁለቱም አስከፊ ኀጢአት የመፈጸም ሁኔታን ያመለክታል።