# ተስፋ ተስፋ አንድ መልካም ነገር ይሆናል ብሎ መጠበቅና የተሻለ ነገር እንደሚመጣ መጠባበቅ ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት “ተስፋ” እግዚአብሔር ለሕዝቡ ቃል የገባውን እንደሚቀበሉ እርግጠኛ ሆ መጠበቅን ነው የሚያመለክተው። ይሁን እንጂ፣ አንድን ነገር እርግጠኛ ሆኖ ወይም በልበ ሙሉነት መጠበቅን የሚያመለክት በመሆኑ ULB በተሰኘው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕም አብዛኛውን ጊዜ፣ “እምነት” ወይም፣ “ድፍረት” ተብሎ ተተርጕሞአል። * አንድን ነገር፣ “ተስፋ ማድረግ” ያን ነገር ለማግኘት መፈለግ ወይም ያ ነገር እንዲሆን መመኘት ነው። * “ተስፋ ማጣት” መልካም ነገር ይሆናል ብሎ አለመጠባበቅ ማለት ነው።