# መንፈስ ቅዱስ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጌታ መንፈስ እነዚህ ሦስት ቃሎች የሚያመለክቱት እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሆነው መንፈስ ቅዱስን ነው። እውነተኛው አንድ አምላክ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ አካላት አሉት። * መንፈስ ቅዱስ አንዳንዴ፣ “መንፈስ” እና “የያህዌ መንፈስ” እና፣ “የእውነት መንፈስ” ተብሏል። * መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በመሆኑ ፍጹም ቅዱስ፣ እጅግ ንጹሕ፣ በባሕርዩና በሚያደርገው ነገር ሁሉ ፍጹም ጻድቅ ነው። * ከአብና ከወልድ ጋር መንፈስ ቅዱስ ዓለምን በመፍጠር ተሳታፊ ነበር። * እግዚአብሔር ወልድ ማለት ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ ሕዝቡን እንዲመራቸው፣ እንዲያስተምራቸው፣ እንዲያጽናናቸውና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ እንዲያስችላቸው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ላከ። * መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን መራው፤ በኢየሱስ የሚያምኑትንም ይመራቸዋል።