# መርሳት፣ ተረሳ “መርሳት” አንድን ሰው ወይም አንድን ነገር ጨርሶ መተው ማለት ነው። “የተረሳ” በሌላው ወገን ጨርሶ የተተወ ግምት ውስጥ የማይገባ ሰው ነው። * ሰዎች እግዚአብሔርን “ረሱ” ከተባለ ለእርሱ ታማኝ አይደሉም፤ ለእርሱ አይታዘዙም ማለት ነው። * እግዚአብሔር ሰዎችን “ረሳ” ከተባለ እርሱ አይረዳቸውም፤ እንደ ገና ወደ እርሱ እንዲመለሱ የተለያየ መከራና ችግር እንዲደርስባቸው ይተዋቸዋል ማለት ነው። * መዘንጋት ወይም የእግዚአብሔርን ትምህርት አለመከተል ማለትም ነው። * “መርሳት” የሚለው ቃል፣ “ረስታችኋል” ወይም “ተረስታችኋል” በሚል የኀላፊ ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል።