# እምነት በአጠቃላይ ደረጃ “እምነት” የሚያመለክተው በእግዚአብሔር፣ በሰው ወይም፣ በነገሮች መተማመንን፣ መደገፍን፣ ወይም፣ መመካትን ነው። * “ማመን” ማለት የምናምነው ሰው የሚናገረውና የሚያደርገው ሁሉ እውነትና አስተማማኝ መሆኑን በሙሉ ልብ መቀበል ማለት ነው። * “በኢየሱስ ማመን” ኢየሱስን በተመለከተ እግዚአብሔር የሚያስተምረውን ሁሉ ማመን ማለት ነው። በተለይም በኢየሱስና ሰዎችን ከኅጢአታቸው እንደሚያነጻቸው ከኅጢአታቸው የተነሳ ከሚጠብቃቸው ቅጣት እንደሚያድናቸው ማመን ማለት ነው። * አንድ ሰው በእውነት በኢየሱስ ካመነ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ውስጥ ስለሚኖር መልካም መንፈሳዊ ፍሬ ወይም የሕይወት ለውጥ ይኖረዋል። * አንዳንድ፣ “እምነት” “የእምነት እውነት” በሚለው በተገለጸው መሠረት፣ በአጠቃላይ ስለ ኢየሱስ የተሰጡ ትምህርቶችን ሁሉ ያመለክታል። * “እምነትን መጠበቅ” ወይም፣ “እምነትን መተው” በሚለው ዐውድ ውስጥ “እውነት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢየሱስን በተመለከተ የተሰጡ ትምህርቶችን ሁሉ ማመንን ነው።