# አካል “አካል” ቃል በቃል የሰው ወይም የእንስሳ ሥጋ ማለት ነው። ይህ ቃል አንድን ነገር ወይም በአንድ ቡድን ውስጥ ያሉ ግለ ሰቦችን ለማመልከትም ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል። * ቃል በቃል ሲወሰድ “አካል” የሞተ ሰው ወይም እንስሳን ይመለከታል። አንዳንዴ “የሞተ አካል” ወይም፣ “ሬሳ” ያመለክታል። * የመጨረዓው የፋሲካ ራት ላይ ኢየሱስ፣ “ይህ ሥጋዬ ነው” በማለት ሲናገር፣ ለኃጢአታቸው ክፍያ ለመሆን. “የሚቆረሰውን” (የሚገደለውን) ሥጋዊ አካሉን ማመልከቱ ነበር። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክርስቲያኖች እንደ አንድ ቡድን፣ “የክርስቶስ አካል” ተብለው ተጠርተዋል። * የሰው አካል ብዙ ክፍሎች እንዳሉት ሁሉ፣ “የክርስቶስ አካል” ብዙ ግለ ሰብ አባሎች አሉት። * በአንድነት እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለእርሱ ክብር እንዲሆን ለማገዝ እያንዳንዱ አማኝ የክርስቶስ አካል ውስጥ የራሱ የሆነ ተግባር አለው። * ኢየሱስ በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች፣ “አካል ራስ (መሪ)” ተብሎአል። የአንድ ሰው ራስ አካሉ ምን ማድረግ እንዳለበት እንደሚናገር ሁሉ፣ እንደ “አካሉ” ብልቶች ክርስቲያኖችን የሚመራና አቅጣጫ የሚያስይዝ ኢየሱስ ነው።