# የስርየት መክደኛ “የስርየት መክደኛ” ከወርቅ የተሠራ ጠፍጣፋ ነገር ሲሆን የታቦቱን የላይኛ ክፍል ለመሸፈን ጥቅም ላይ ይውል ነበር። አንዳንድ ትርጉሞች “የስርየት መሸፈኛ” ይሉታል * የስርየት መክደኛ 115 ሳንቲሜትር ርዝመትና 70 ሳንቲሜትር ስፋት ነበረው * ከስርየት መክደኛው በላይ ክንፎቻቸው እርስ በርስ የተነካኩ ሁለት የወርቅ ኪሩቤል ነበሩ * ከስርየት መክደኛው በላይ፥ ከተዘረጉት የኪሩቤል ክንፎች በታች ከእስራኤላውያን ጋር እንደሚገናኝ ያህዌ ተናግሮአል። እንደሕዝቡ ተወካይ ይህን ማድረግ የተፈቀደለት ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር * ይህ የስርየት መክደኛ አንዳንዴ፥ “የምሕረት መቀመጫ” ተብሎአል፤ እንዲህ የተባለበት ምክንያት ኃጢአተኛ የሰው ልጆችን ለመዋጀት የሚመጣው የእግዚአብሔር ምሕረት መተለለፊያ ስለሆነ ነው