10 lines
1.2 KiB
Markdown
10 lines
1.2 KiB
Markdown
|
# መሰናከያ፣ መሰናከያ ዐለት
|
||
|
|
||
|
“መሰናከያ” ወይም፣ “መሰናከያ ድንጋይ” አንድ ሰው ተደናቅፎ እንዲወድቅ የሚያደርግ ነገርን ያመለክታል
|
||
|
|
||
|
* አዲስ ኪዳን ውስጥ ይህ ቃል ተሰናክሎ ውስጡ የወደቀ እንስሳ ላይ እንዲዘጋ ወጥመድን ወይም አሽክላን የሚያስፈነጥር ልምጭ ወይም ሌላ ነገር ያመለክታል
|
||
|
* ምሳሌያዊ መሰናከያ አንድ ሰው በግብረ ገባዊ ወይም በመንፈሳዊ መልኩ እንዲወድቅ የሚያደርግ ማንኛውም ነገር ማለት ነው
|
||
|
* በመሳሌያዊ መልኩ፣ “መሰናከያ” ወይም፣ “መሰናከያ ድንጋይ” አንድ ሰው በኢየሱስ እንዳያምን ወይም በመንፈሳዊ ሕይወቱ እንዳያድግ የሚያግድ ነገርን ያመለክታል
|
||
|
* አብዝኛውን ጊዜ እንደመናከያ የሚሆነው አንድ ሰው ራሱ ወይም ሌላው የሚያደርገው ኅጢአት ነው
|
||
|
* አንዳንዴ እግዚአብሔር ራሱ በእርሱ በሚያምፁ ሰዎች መንገድ ላይ መሰናከያ ያደርጋል
|