# ሙሴ ወንዶቹ በምድሪቱ ስለሚኖሩ ሰዎች ምን እንዲሰልሉ ነገራቸው? ሙሴ ለወንዶቹ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ጠንካሮች ይሁኑ ደካሞች፣ ጥቂት ይሁኑ ብዙ እንዲሰልሉ ነገራቸው፡፡ # ሙሴ ስለ ምድሪቱ ከተሞች ምን እንዲመለከቱ ለሰላዮቹ ነገራቸው? ሙሴ ከተሞቹ እንደ ጦር ሰፈር ሆነው የተቀጠሩ ከተሞች መሆን አለመሆናቸውን እንዲመለከቱ ነገራቸው፡፡ # ሙሴ የላካቸው መሪዎች ስለ ምድሪቱ ምን እንዲያውቁ እና ምን ይዘው እንዲመለሱ ነገራቸው? ሙሴ ለመሪዎቹ ምድሪቱ ሰብል ታበቅል እንደሆነ፣ነዛፎች ያሉባት መሆኗን፣ እና ከምርቶ ከየአይነቱ ጥቂት ይዘው እንዲመጡ ነገራቸው፡፡ # ሰላዮቹ ከኤሽኮል ሸለቆ ምን ቆርጡ? ሰዎቹ ኤሽኮል ሸለቆ ሲደርሱ፣ የወይን ዘለላ ያንዠረገገ ቅርኝጫፍ ቆረጡ፡፡ # የተንዠረገገውን የወይን ዘለላ ለማምጣት ስንት ሰዎች አስፈለጉ፣ ደግሞስ ሰዎቹ ሌላ ምን ይዘው ተመለሱ? በመሎጊያ ተሸክመው ለማምጣት ሁለት ሰዎች አስፈልገው ነበር፤ ቡድናቸው ሮማን እና በለስም ጭምር አመጡ፡፡