# ሦስቱ የዳዊት ዝነኛ ወታደሮች የዳዊትን መሻት ለማሙዋላት ምን አደረጉ? ሦስቱ ዝነኛ የዳዊት ወታደሮች የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ሰፈር ጥሰው በማለፍ ከቤተልሔም የጒድጓድ ውሃ ቀዱና ለዳዊት ይዘውለት መጡ። # ዳዊት ከቤተልሔም የጒድጓድ በነፍሳቸው ቈርጠው ያመጡትን ውሃ አልጠጣም ያለው ለምንድነው? ዳዊት ውሃውን መጠጣት ያልፈለገበት ምክንያት በነፍሳቸው ቈርጠው የሄዱትን የእነዚያን ኀያላን ሰዎች ደም እንደ ጠጣሁ ይቈጠራል በማለት ነበር።