# የመጽሐፉ ቀጣይ ክፍል የተጻፈው ለየትኛው መልአክ ነው? የመጽሐፉ ቀጣይ ክፍል የተጻፈው በሰምርኔስ ላለው የቤተ ክርስቲያን መልአክ ነው [2:8] # በሰምርኔስ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ምን ገጥሞት ነበር? በሰምርኔስ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን መከራ፣ ድኽነትና ስድብ ገጥሞት ነበር [2:9]