# ሕዝቡ ለያህዌ ባይታዘዙ ምንም ተስፋ የላቸውም ማለት ነው? ሕዝቡ ኅጢአታቸውን፣ የአባቶቻቸውን ኀጢአትና ክህደታቸውን ቢናዘዙ፣ ልባቸውንም ቢዋረድና የኀጢአታቸውን ቅጣት ቢቀበሉ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የገባውን ኪዳን እንደሚያስብ ያህዌ ይናገራል፡፡ # ምንም እንኳ ኀጢአት ቢያደርጉም ያህዌ የሰጣቸው ተስፋ ምንድነው? ፈጽሞ እስኪያጠፋቸው ድረስ እንደማይተዋቸውና እንደማይጸየፋቸው ያህዌ ቃል ይገባል፤ ኪዳኑን በማሰብ አምላካቸው ይሆናል፡፡